በአንድ እጅ መፀሐፍ ቅዱስ በአንድ እጅ የብሄር አጀንዳ አይሆንም

“መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
የተወዳቹ ቅዱሳን ሰሞኑን በተለያዩ ማሀበራዊ ሚዲያዎች የቤተክርስቲያናችን መስራች እና ባለራዕይ ሐዋሪያው አስራኤል ዳንሳ አገልግሎት እና ቤተክርስቲያኗ ላይ በተደራጀ መልኩ የስም ማጥፈት ዘመቻ ተከፍቷል ይህን ሁኔታ ተመልክተን ወደህግ ከመሄድ ይልቅ የችግሩን ምንጭ ማጣራት ቅድሚያ ሰተን መመልከትን መረጥን ሆኖም ቅድሚያ ሰጠን ስናይ የድርጊቱ ዋና ተዋናዬችም ከዚህ ቀደም በቤተ/ክኗ በተለያየ ስፍራ ሲያገለግሉ የነበሩ ወንድም እና እህቶች በተለያዩ ጊዚያት ክርስቲያናዊ ምግባር ያልሆኑ ለሀገርም አጥፊ የሆነን በክርስቶስ አንድ ሆነን ሳለ የብሄር አጀንዳ ሲያነሱ ከአገልግሎት የታገዱ ሆነው አገኘናቸው የዚህ እኩይ ስራ ባለቤት ጠላታችን ሴጣን በመሆኑ ይህን ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል ሆኖምግን ከጥፋታቸው ከመመለስ ይልቅ ችግሩን ሌላ መልክ በማስያዝ ድብቅ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም አሁን በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ ጭምር እምነትን ተገን አርገው ለማጨናገፍ ከጀርባቸው ባለ ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ህግ በሀገር የሌለ በማስመሰል የህግ አስከባሪዎችን ጭምር ስም በማጥፋት እና መንግስት ባለበት ሀገር አንድን አገልጋይ የግል እስርቤት አለው የሚል በሬ ወለደ ይሉት ትርክ ውስጥ ገብተዋል:: ስለሆነም ከዚህ በኋላ ጉዳዩ እየተባባሰ ሄዶ እንደ እቅዳቸው በሌሎች የእምነት ተቋማት እንደተከሰተው አይነት እኩይ ተግባራት ከመፈፀማቸው በፊት ወደ ህግ ልንሄድ ግድ ብሎናል ከዚህ በኋላ ያለውን የህግ ሂደት ተከታትለን የምናሳውቃችሁም ይሆናል:: 
የኢየሱስ ድንቅ ስራ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ቦርድ

Leave a Reply

%d bloggers like this: