ትንቢትን አትናቁ

………….ትንቢትን አትናቁ……

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ህያው ታሪኮችን በውስጡ ያካተተ ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ ዘመን የማይሽረው ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህንንም ሀሳብ ሉቃስ በወንጌሉ የመጀመሪያ ምዕራፉ እንዲህ ያስረዳናል
የሉቃስ ወንጌል 1
1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።

ክርስቲያኖች መመሪያችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ እንደዚህ ሲሆን ሁኔታ እንዳለው ወይም ሰው እንዳለው ሳይሆን ቃሉ እንዳለው ነገሮችን መመዘን የምንችልበት ሙሉ ማንነት ይኖረናል ይህ ካልሆነ ግን እመኑኝ የመጣው ንፋስ ሁሉ ማለት ይቻላል ይወስደናል፡፡

…….ትንቢት ሲነገር ከባድ ሲፈፀም ግን ቀላል ይሆኑብናል ………

እግዚአብሔር አምላክ በተለያዩ ጊዜዎች በነቢያቱ ፤ በሐዋሪያቱም በብዙና በተለያዩ መንገዶች የሚመጣውን ሁሉ በትንቢት ገለጠ፡፡ የዕብራዊያን ጸሐፊ መጽሐፉን ሲጀምር ይህን ሃሳብ አብራርቶልናል፡፡
ወደ ዕብራውያን 1
1 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥

2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤

በአብዛኛው ትንቢት ሲነገር አንድ ጠንካራ፤ከባድና ጥብቅ ቋጠሮ ነው፡፡ ሲፈፀም ግን እስከመጨረሻው ቀላል እስከሚባለው ጫፍ ድረስ እጅግ ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ በመንፈሳዊ ቋንቋ የተነገረንን ወደ ሥጋዊ ፍጻሜ መተርጎም ምን ማለት እንደሆነ ማሰብ ነው፡፡ በዓይን ያዩትን ድርጊት እንኳ በጹሐፍ በቃላት ለመግለጽ ቀላል አይደለም፡፡ 
አንድ ትንቢት ለሳምንታት ፤ለበወራት ፤ ለዓመታት ሊነገርና ሊፈፀም ይችላል፡፡ የትንቢቶችን አፈጻጸም ማወቀቅ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፤19-22 መንፈስን አታጥፉ፤ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።

ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል!!!!

Leave a Reply

%d bloggers like this: