እነዚህ ክርስቲያኖች

*************እነዚህ ክርስቲያኖች በአእምሯቸው ህፃናት ነበሩ**************
20 ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
ህፃን ማለት ያላደገ ወይም ያልበሰለ ማለት ነው፡፡በመሆኑም እግዚአብሔር ከእርሱ የተወለዱት ሁሉ በአእምሮአቸው ያላደጉ ወይም ያልበሰሉ ይሆኑ ዘንድ ስለማይሻ “በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ”
በማለት ህዝቡን ይመክራል፡፡ በእግዚአብሔር ሃሳብ ጥልቀት ያልተሞላ እንዲሁም ክፉን ከመልካሙ ለይቶ ወይም አመዛዝኖ መኖር ያልቻለ ሁሉ አእምሮው ህፃን አእምሮ ነው፡፡ በእርግጥ መንፈሳዊ ህፃንነት እና የአእምሮ ህፃንነት አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች መንፈሳዊ ህፃናት ስለነበሩ ሐዋሪያው እንዲህ በማለት ይነግራቸው ነበር፡-
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3
1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
2 ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤

3 ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?
4 አንዱ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም። እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?

እነዚህ ክርስቲያኖች በአእምሯቸው ህፃናት ነበሩ፡፡ የአእምሮ ህፃንነት ከመንፈሳዊ ህፃንነት ጋር የተያያዘ ስለሁነ ህፃንነቱ የእድሜ ጉዳይ ሳይሆን ህፃንነት ያላደገ አመለካከት ነው፡፡ ህፃንነት አካላዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህፃንነትም ሆነ አእምሯዊ ህፃንነት የባህሪያ ጉዳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ በህሪ ያላደገ መንፈሳዊ ህፃን እንደሆነ ሁሉ በአእምሮውም ያላደገ እንዲሁ ያላደገ ሀሳብ እና ምግባር መታወቂያወቹ ይሆናሉ መለት ነው፡፡ በአእምሮ ህፃን የሆኑ ሰዎች ወይም ቤተክርስቲያን ምን አይነት ባህሪያቶች እንደሚታዩባቸው እና ምን አይነት የህይወት አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ ከዚህ ቃል እንረዳለን፡፡
14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4  
ህፃን ሆኖ የመቅረት ጉዳቱ፡-በቀላሉ ይታለላል፤ አቋም የለውም፤ የከበረውን ከተዋረደው የማይለይ በዚህም ምክኒያት ለተራ ነገር ይማረካል፤ ለስህተቶች የተጋለጠ ነው፤ የጠላትን ተንኮል መለየት የሚችልበት አቅም አይኖረውም፡፡ በአጠቃላይ ህፃንነት ካልተሻረ አደጋው ብዙ ነው፡፡
የዛሬውን ሃሳቤን በዚህ ቃል እቋጫለሁ 
11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13
*******************ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል***************

Leave a Reply

%d bloggers like this: