እውነተኛ ንስሐ

*** እውነተኛ ንስሐ ካደረግን የቀደመውን ልምምዳችንን ለመተው ሙሉ አቅም እናገኛለን***

እውነተኛው ለውጥ የሚመጣው እውነተኛውን ማንነታችንን ስንደርስበት ነው! ለውጥ የሚጀምረው ከማመን ነው ! ወገኞቼ አብዛኛውን ጊዜ ስለንስሃ ሲነገረን የባህሪ ለውጥ ማድረግ እንደሆነ አድርገን እንወስዳለን፡፡ ነገር ግን እንደዛ አይደለም ፤ የባህሪ ለውጥ የንሐ ፍሬ ነው እንጂ፡፡ ታዲያ ወዳጆቼ እውነተኛ ንስሐ ካልተሃሄደ ፤ የባህሪ ለውጡ ዘለቄታ አይኖረውም፡፡ ለዚህም ምሳሌ በየሰፈራችን በርካቶች አሉ ………
14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። የማርቆስ ወንጌል 1
ልክ እንደ ፅድቅ፤ ንስሐም ከማመን ጋር ተያይዞ እንደተፃፈ እንመለከታለን፡፡
10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና…..ወደ ሮሜ ሰዎች 10 “ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ የማርቆስ ወንጌል 1” 

ንስሐ የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያመጣ ውሳኔ ነው፤ይህ ደግሞ ወደ ዓላማ እና ተግባር ለውጥ ያመራል፡፡ ንስሐ መስበክ ማለት ለሰዎች ወንጌልን መስበክ ሲሆን፤ በወንጌል ማመን ሲጀምሩ ኃይሉን መለማመድ ይጀምራሉ፡፡ ወገኖቼ እውነተኛ ንስሐ ካደረግን የቀደመውን ልምምዳችንን ለመተው ሙሉ አቅም እናገኛለን፡፡ የዛሬውን ሃሳቤን በዚህ ቃል አገባድዳለው…

8 ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ። ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው።
9 ስላጠመዱት ዓሣ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩ ሁሉ ተደንቀዋልና፥
10 እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ባልንጀሮች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን። አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ አለው።
11 ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት። የሉቃስ ወንጌል 5

*********************ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል*********************************

Leave a Reply

%d bloggers like this: