እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል


19-20 ልባችንም በእኛ ላይ በሚፈርድበት ሁሉ፥ ከእውነት እንደ ሆንን በዚህ እናውቃለን በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3
አንዳንድ ሰዎች ከተለያዩ ገጠመኞች የተነሳ (በልጅነታቸው ከደረሰባቸው ነገር የተነሳ) የኃጢአት ልምምድ ሊኖራቸው ይችላል፤ ታዲያ የሚያስፈልጋቸው ፈውስ እንጂ ኩነኔ አይደለም፡፡ አሁን የመንጋው እረኞች እንደመሆናችን፤ በዚህ ምድር ያለነው ልንረዳቸው እንጂ ልንኮንን ወይንም ልንፈርድባቸው አይደለም፡፡ ይህንን እውነት ደግሞ መጽሐፍ በግልፅ ያስረዳናል፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ እኛ እንድንረዳቸው ይረዳናል፤ እርሱ በእስራታቸው ውስጥ እንዴት እየተሰቃዩ እንዳሉ ያያልና፡፡ ነገር ግን በሕይወታቸው ላይ ለውጥ የሚያመጣ የግል ጥረታቸው አይደለም ፤ክርስቶስ በእነሱ ውስጥ እና እነርሱም በእርሱ ማን የመሆናቸው እውነታ እንጂ፡፡
32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

33 እነርሱም መልሰው። የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ። አርነት ትወጣላችሁ እንዴት ትላለህ? አሉት።
34 ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።
35 ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል።

36 እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ።የዮሐንስ ወንጌል 8

በመግቢያው ላይ ወዳለው ጥቅስ እንመለስ፡፡ ቁጥር 19 “በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን” ይላል በሌላ አማረኛ ልባችንን በእርሱ ፊት እርፍ እንዲል እናደርጋለ፡፡ በኩነኔ የተሞላን ስንሆን፤ ልባችን በእግዚአብሔር ፊት ያረፈ አይደለም፡፡ ወደ ቤተ-ክርስቲያንም የሚመጡ በርካታ ሰዎች በሰሩት ሀጢአት ልባቸው እየኮነነቻቸው ነው የሚመጡ፡፡ ታዲያ በእነዚህ ሰዎች ላይ መፍረድ ሳይሆን እንደ ክርስቲያን መንገድ መሳየት ነው ያለብን፤ ክርስቶስን ወደ ውስጣቸው እንዲያስገቡ መድረግ፡፡

ወደ ሮሜ ሰዎች 8
1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።

3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው።
4 መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።

5 ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።

6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤
7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።
8 ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።
10 ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
11 እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።የዮሐንስ ወንጌል 8

********ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል*****

Leave a Reply

%d bloggers like this: