ውድ የሀገሬ ህዝቦች !!!

ውድ የሀገሬ ህዝቦች በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የምትገኙ ሰላማችሁ ይብዛ !!! ዛሬ ያለሁበትን ሁኔታ ላሳውቃችሁ በፅሁፍ ወደ እናንተ መጥችያለሁ: ፡ እንደሚታወቀው እኔ ሐዋሪው እስራኤል ዳንሳ ጌታ ለአገልግሎቱ ከመረጠኝ ጊዜ አንስቶ እስካሁን እስከዚህች ሰዓት ድረስ እኔን ተማምኖ ሳሆይን እራሱን ተማምኖ ፀጋውን የሰጠኝን አምላኬን በቅንነት እያገለገልኩ ነው ፤ ያለ ምክኒያት የወደደኝን አምላኬን ነገም እስከ ህይወቴ ፍፃሜ አገለግለዋለሁ ፡፡ 

ወደ ዋናው መልዕክቴ ስገባ፡- ባለፈው ስለ 265 የኢየሱስ ድንቅ ስራ ቤ/ያን አጥቢያ እና በውስጧ ስለሚያገለግሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮቹዋ ችግር ላይ ወድቀዋል፤ በሁሉም አጥቢያዎች ያለው የባንክ አካውንት የግሌን ጨምሮ ገንዘብ እንዳናንቀሳቅስ ተደርገናል ብዬ ቪዲዮ መልቀቄ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ቪዲዮ ስለቅ ጩሄታችንን ለሚመለከተው አካል እንድታደርሱ ብዬ እንደ መሪ የአባትነት ሚናየን አድርግያለሁ፡፡ 

ወደ ሀሳቤ ስመለስ እስካሁንም በህጋዊ መልኩ እየተንቀሳቀስን የተፈጠሩ ነገሮችን ለመፍታት ወደ ተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ገብተናል፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን ከቤ/ያኗ ስፍት እና በውስጧ ከሚያገለግሉ የአገልጋዮች ብዛት ወቅቱን ያገናዘበ ምላሽ አልተሰጠም፡፡ በዚህም ምክኒያት የአምልኮ ስፍራ የኪራይ ገንዘብ እንዲሁም የአገልጋዮች ደሞዝ መክፈል በፍፁም አልቻልንም፤ ከዚህም የተነሳ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ያሉ አገልጋዮች የከፋ ችግር ላይ ወድቀዋል፡፡ ስለዚህ በያላችሁበት ቦታ በፀሎታችሁ ገጎናችን እንደቆማችሁ ሁሉ አሁንም ቀጥሉበት እያልኩ ፡ አንድ ግልፅ አድርጌ የማልፈው ነገር ይኖራል እሱም ባለፈው የተለያዩ አካላት በውል የማናውቃቸው የፖሊስ የድንብ ልብስ በመልበስ ገንዘብ ይጠይቁኛል የተለያዩ ነገሮችን እድገዛላቸውም ጭምር ይጠይቁኛል ብዬ ነበር፡፡ አሁን ግን እነዚህ የህግ አግባብ እስካልተከተሉ ድርስ የህግ ሰዎች ሊሆኑ ስለማይችሉ፤ ደግሞም 24 ሰዓት ህግን ለማስከበር ደፋ ቀና የሚሉ የህግ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በእነሱ ስም የተለያዩ ስራዎችን የሚሰሩ አሉ ፡፡ ስለሆነም መንግስት በእንደዚህ አይነት ስራ ላይ በተሰማሩት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አምናለሁ፡፡ ስለሆነም በባለፈው ንግግሬ ላይ ያጠፋሁት ነገር ካለ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ልጠይቅ እወዳለሁ ይንንም ያደረኩት አሁንም ከህጋዊ የመንግስት አካል የደረሰብን በደል ስለሌለ ነው፡፡ 
************ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል*****************

Leave a Reply

%d bloggers like this: