የኢያሪኮ እንቅስቃሴ

የኢያሪኮ እንቅስቃሴ የእምነት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች “መውረሳችን አይቀርም ፤ምድሪቱን እንወርሳለን አሁን ማድረግ ያለብን ማመንና መታዘዝ ብቻ ነው” የሚሉ ናቸው፡፡
ዕረፍትና ርስትን መውረስ አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ዕረፍት ነው፡፡ አሁን ለትውልዱ የቀረለት ዕረፍት ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሰንበት ነው፡፡
ዕረፍት፡- ክርስቶስ እግዚአብሔርን እና እኛን ያረካ ፍፁም የሆነ ሰንበት(ዕረፍት) ነው፡፡ ጌታ እራሱ የራሱን የውስጥ ዕረፍትን ሊያወርሰን ይሻል፡፡ አለማረፍ ወይም መጨነቅ መየትነውም መልኩ ቢታይ የመሸነፍ ምልክት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ላይ እምነት እንዲኖረን ያስፈልጋል ፡፡ ረአብ በማመን የአብርሐምን ዘርተቀላቀለች፡፡
ወደ ዕብራውያን 11፥31

ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም። 

ዛሬም ይህ ትውልድ በእምነት በኩል መግባት ወዳለበት መንፈሳዊ ክልሎች ሁሉ እንዲገባ እግዚአብሔር ይሻል፡፡
ወደ ዕብራውያን 12
1-2 እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።

********ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል*********

Leave a Reply

%d bloggers like this: