ጸጋ ያልተገባን፤ ልናገኘው የማይገባ እና ዋጋችን ያልሆነ የእግዚአብሔር ሞገስ ነው

…..ጸጋ ያልተገባን፤ ልናገኘው የማይገባ እና ዋጋችን ያልሆነ የእግዚአብሔር ሞገስ ነው……
ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን? በማለት ነው ማቴዎስ ከስር ባለው ጥቅስ የሚያበቃው
የማቴዎስ ወንጌል 20
1 መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።
2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።

3 በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥

4 እነዚያንም። እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።
5 ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።

6 በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና። ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው።
7 የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት። እርሱም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው።
8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን። ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው።
9 በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።

10 ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
11-12 ተቀብለውም። እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።
13 እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን?
14 ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?
15 ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?

ቀኑን ሙሉ ሲሠሩ የነበሩት ጥቂት ጊዜ ብቻ ለሠሩት ከእነርሱ እኩል ስለከፈላቸው በአትክልት ስፍራ ባለቤቱ ደስ አልተሰኙም ነበር፡፡ እነርሱ ረጅም ሰዓት ስለሰሩ የበልጥ ሊከፈላቸው እንደሚገባ ተሰማቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ስለ ፀጋ ልናያቸው የምንችል እውነታዎች አሉ፡፡ የቀደሙት ሠራተኞች ጸጋን አልተቀበሉም ፤ የተቀበሉት ደሞዛቸውን ፤ ያገኙት የሰሩተን ያህል ነው፡፡ ኋላ ልይ የመጡት ግን የተቀበሉት ሁለቱንም ደሞዝም ጸጋም ነው፤ ከሰሩት በላይ ተቀበሉ፡፡ ጸጋ፡- ያልተገባን ፤ ልናገኘው የማይገባን እና ዋጋችን ያልሆነ ነው፤ ወንጌሉ ራሱ የጸጋ ወንጌል ተብሎ ተጠርቷል፡፡
የሐዋርያት ሥራ 20፡24 ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ

ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡6 በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።

የዳንነው በጸጋ ነው ፤ የተፈወስነው በጸጋ ነው ፤ ወደ አገልግሎት የገባነው በጸጋ ነው እናም በአገልግሎት ውስጥ እግዚአብሔር የሚጠቀምብን አሁንም በጸጋ ነው!………

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል !!!!!!

Leave a Reply

%d bloggers like this: